መዝገብህ ያለው ዬት ነው? ምድር ላይ ነው ወይስ ሰማይ ላይ ነው?
ስለእግዚአብሔር ጽድቅ፣ ስለእግዚአብሔር መንግስት፣ ስለደኅንነትህ፣...... እንቅልፍ ነስቶህ ያውቃል❓
በውኑ በእግዚአብሔር ቃል ታምናለህ? በትክክል መንግስተ ሰማይ እንዳለና በትክክል ገሃነም እንዳለ ታምናለህ?
ኃጢአት ያለበት ዘላለማዊ ፍርድ በሆነው በገሃነም እሳት ከዘላለም እስከ ለዘላለም እየተቃጠለ እንደሚኖር ታምናለህ?
ጌታ ኢየሱስ አንተን ከገሃነም ሊያድንህ በውኃና በደም እንደመጣ(1ዮሐ5፥6) ታምናለህ?
ኢየሱስ በውኃና በደም መጣ ማለት ምን ማለት ነው?
የእግዚአብሔር ጠላት የሆነው ሰይጣን አንተን በኃጢአት ጥሎ ለዘላለም ሞት ያዳረገህ መሆኑን ታምናለህ?
አንተ እዚህ ምድር ላይ ኃጢአተኛ ሆነህ የተወለድክ ከዚህ ምድር እስከሚትለይ ኃጢአትን የሚታደርግና በኃጢአትህ የዘላለምን ሞት ለመሞት የታጨህ ጎስቋላ ሰው መሆንህን ታምናለህ?
የእግዚአብሔርን መንግስት እንዴት ነው የምገባው? ብለህ ለዚያ ሰርተህ ታውቃለህ❓
እዚህ ጋር "ሰርተህ" ስልህ አስራትና በኩራት፣ ምጽዋት፣ ጾምና ጸሎት፣ ለድሆች መስጠት፣ በሆነ ክርስትና ኃይማኖት ስር ስለመጠለል፣...... እያልኩህ አይደለም።
ምንም ስለኃጢአትና ስለጽድቅ፣ ስለእግዚአብሔር መንግስት፣...... ግድ የማይልህና የማያሳስብህ ልብህ በምድራዊ ነገር ከብዶና ደንዝዞ ስላለ ነው። ልብህ ምድር ላይ ያለው መዝገብህ ምድር ላይ ስላለ ነው።
ይህ ማለት አንተ ኃጢአተኛ ሆነህ መወለድህን የማታምንና ከኃጢአትህ በአንድ ጊዜ መዳን የማትፈልግ ነህ ማለት ነው። ስለዚህ አንተ ወደ ገሃነም ትጣላለህ ማለት ነው።
ገሃነም ሲባል ምንም የማትፈራው ምድራዊ ስለሆንክ ነው። ምድራዊ ነህ ማለት ከዱር አራዊት፣ ከእንስሳትና ከእጽዋት አትሻልም ማለት ነው።
አሁንም ተንቀሳቀስ ገሃነም ከፊትህ አለ፤ ገና ወደ ገሃነም አልገባህም፣ ዕድልና ጊዜ አለህና ካለህበት ከክፉ መንገድ ተመለስና የእውነትን መንገድ ተከተል።
ይህ የእውነት መንገድ የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚሰብከው የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው። ወደዚህ ወንጌል ተመለስ! ያኔ የእግዚአብሔርን መንግስት ትወርሳለህ።(ዮሐ3፥5)
www.nlmethiopia.com
-
t.me/tobebornagain